Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ባለፉት 11 ወራት ከ700 ሺህ በላይ ዲጂታል የነዋሪነት መታወቂያ መሰጠቱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በመዲናዋ ባለፉት 11 ወራት ከ700 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ዲጂታል የነዋሪነት መታወቂያ መስጠቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ገለጸ፡፡

ኤጀንሲው በበጀት ዓመቱ ያከናወናቸውን የዕቅድ አፈፃጸምና ተቋማዊ የማሻሻያ እርምጃዎችን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙኃን ማብራሪያ ሰጥቷል።

የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር በረከት በቀለ÷ኤጀንሲው ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረገ የአሰራር ማሻሻያ በማድረግ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ተደራሽ እያደረገ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በዚህም በከተማ አስተዳደሩ በ105 ወረዳዎች ላይ ምቹ የስራ አካባቢ በመፍጠርና ነዋሪዎች በጤና ተቋማት ጭምር የወሳኝ ኩነት አገልግሎትን በቅርበት እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑን አብራርተዋል።

በተጨማሪም ለአቅመ ደካሞችና ተንቀሳቅሰው አገልግሎት ማግኘት ለማይችሉ ሰዎች የቤት ለቤት አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑንም መጠቆማቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የቴክኖሎጂ አሰራር ሥርዓቱም በ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት ባለፉት 11 ወራት 1 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር የሚገመት የመንግስትና ህዝብ ሃብትን ከብክነት ማዳን እንደተቻለ አስረድተዋል።

በበጀት ዓመቱ 11 ወራት ለ715 ሺህ 872 ዜጎች የዲጂታል መታወቂያ መሰጠቱንም ተናግረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.