Fana: At a Speed of Life!

ምንጩ ያልታወቀ ንብረት መውረስን መሠረት ያደረገው ረቂቅ አዋጅ ከግለሰቦች ሕገ መንግስታዊ መብቶች ጋር እንዲጣጣም ሆኖ የተዘጋጀ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በህገወጥ መንገድ የተፈራን ሃብት ወይንም ምንጩ ያልታወቀ ንብረት መውረስን መሠረት ያደረገው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅ ከግለሰቦች ሕገ መንግስታዊ መብቶች ጋር እንዲጣጣም ሆኖ የተዘጋጀ ነው ተባለ።

በረቂቅ አዋጁ ላይ ሃሳባቸውን ያጋሩን የህግ ምሁሩ አቶ ማሩ አብዲ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እየታየ የሚገኘው ረቂቅ አዋጁ ተግባራዊ መሆን ሲጀምር በኢትዮጵያ ወንጀል አትራፊ መሆኑ እንዲቆም ትልቅ ሚና ይጫወታል ብለዋል።

ረቂቅ አዋጁ በወንጀል የተገኘን ሃብት ከማስመለስ ባለፈ በህጋዊ መንገድ ለተገኘ ማንኛውም ሃብትና ንብረት ዋስትናን የሚሰጥ መሆኑንም አመላክተዋል።

ረቂቅ አዋጁ እንግዳ ያልሆነ ቀደም ሲል በሀገር ውስጥ እና በሌሎች ዓለም ሀገራት ተግባራዊ እየተደረገ ነው ያሉት ማሩ አብዲ በኢትዮጵያ በወንጀል የተገኘ ሃብትን ለማስመለስ እየተከናወኑ ያሉ የህግ ማዕቀፍ ዝግጅት ስራዎች እና ጠንካራ የአስፈፃሚ አካላት ግንባታ ሂደት ማሳያ መሆኑንም ተናግረዋል።

በመራኦል ከድር

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.