Fana: At a Speed of Life!

በቢሾፍቱ በሚገኙ የውጭ ኩባንያዎች የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት በትኩረት ይሰራል – ኮሚሽኑ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢስተርን ኢንዱስትሪ ፓርክ እና በቢሾፍቱ አካባቢ የሚገኙ የውጭ ኩባንያዎች የገጠሟቸውን ችግሮች ለመፍታት በትኩረት እንደሚሰራ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ሃና አርዓያስላሴና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በኢስተርን ኢንዱስትሪ ፓርክ እና በቢሾፍቱ አካባቢ የሚገኙ የውጭ ኩባንያዎችን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝታቸውም÷ በፍሬንድሺፕ ፍላወርስ፣ ጆይቴክ፣ ሆላንድ ዴይሪ፣ ሪፍትቫሊ የውሃ ቴክኖሎጂ ድርጅት እንዲሁም በኢንዱስትሪ ፓርክ የሚገኘውን ዩኒሊቨር ድርጅት ተመልክተዋል፡፡

ሃላፊዎቹ በድርጅቶቹ ያለውን የሥራ እንቅስቃሴ ተዘዋውረው በመመልከት መገምገማቸውን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

የድርጅቶቹ ባለቤቶችና ተወካዮች በአጠቃላይ የድርጅቶቹን የሥራ እንቅስቃሴ እና የገጠሟቸውን አንዳንድ ችግሮች አንስተዋል፡፡

ኮሚሽነር ሃና አርዓያስላሴ÷ ድርጅቶቹ የገጠሟቸውን ችግሮች ለመፍታት ኮሚሽኑ የማያቋርጥ ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.