Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ፍሬወይኒ የ1500 ሜትር የሴቶች ሩጫ ውድድር አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ፍሬወይኒ ሐይሉ በፖላንድ በተካሄደው የ1500 ሜትር የቤት ውስጥ የሴቶች ሩጫ ውድድር አሸንፋለች፡፡

አትሌቷ በፖላንድ ባይድጎሽ ከተማ በተካሄደው የ1500 የሴቶች ሩጫ ውድድር 3፡58.59 በሆነ ሰዓት በመግባት ማሸነፏን ከዎርልድ አትሌቲክስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከዚህ በፊት አትሌቷ በፖላንድ ባደረገችባቸው ውድድሮች ጥሩ ሰዓት በማስመዝገብ በተደጋጋሚ ማሸነፏ የሚታወስ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.