Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ 2 ሽልማቶችን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአፍሪካ ምርጥ የበረራ ላይ መዝናኛና የበረራ ላይ ገመድ አልባ ኢንተርኔት አገልግሎት ሽልማት አሸናፊ ሆነ፡፡

በዓመታዊው የ“ኤየርላይን ፓሴንጀር ኤክስፔሪያንስ አሶሴሽን“ (አፔክስ) በተባለ የ2024 የደንበኞች ምርጫ ሽልማት ላይ ዓየር መንገዱ ፥ የአፍሪካ ምርጥ የበረራ ላይ መዝናኛ እና የአፍሪካ ምርጥ የበረራ ላይ ገመድ ዓልባ ኢንተርኔት አገልግሎት ተሸላሚ መሆኑን አስታውቋል፡፡

አፔክስ ፥ የመንገደኞችን ድምፅ መሰረት በማድረግ ለዓየር መንገዶች ዕውቅና የሚሰጥበት መድረክ በአቪዬሽን ኢንደስትሪው ትልቅ ስፍራ ከሚሰጣቸው ሽልማቶች አንዱ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በተጨማሪም በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ ዓየር መንገዶች ለሚያቀርቡት የላቀ የደንበኞች አገልግሎት ዕውቅና የሚሰጥበት መሆኑን ከአየር መንገዱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.