Fana: At a Speed of Life!

ፋሲል ከነማ ሻሸመኔ ከተማን 2 ለ 1 አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ28ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፋሲል ከነማ ሻሸመኔ ከተማን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

የፋሲል ከነማን የማሸነፊያ ግቦች ፍቃዱ አለሙ በጨዋታ እና በፍጹም ቅጣት ምት አስቆጥሯል፡፡

ሻሸመኔ ከተማን ከሽንፈት ያላዳነችዋን ብቸኛ ግብ ደግሞ ሁዛፍ አሊ ከመረብ አሳርፏል፡፡

በተመሳሳይ በፕሪሚየር ሊጉ መርሐ ግብር ምሽት 12 ሰዓት ላይ ሐዋሳ ከተማ እና ወልቂጤ ከተማ ባደረጉት ጨዋታ አቻ 2 ለ 2 በሆነ ውጤት ተለያይተዋል፡፡

የሐዋሳ ከተማን ጎሎችን አብዱልባሲጥ ከማል እና ዓሊ ሱሌይማን ሲያስቆጥሩ የወልቂጤ ከተማን ሁለት ግቦች ደግሞ ጋዲሳ መብራቴ አስቆጥሯል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.