Fana: At a Speed of Life!

በጋምቤላ ክልል መሬት ወስደው ያላለሙ ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃዳቸው ተሰረዘ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)በጋምቤላ ክልል በእርሻ ኢንቨስትመንት መሬት ወስደው ያላለሙ 54 ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃዳቸው መሰረዙን የክልሉ ኢንቨስትመንት ቦርድ አስታወቀ፡፡

የኢንቨስትመንት ቦርዱ ሰብሳቢና የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ እንዳሉት፥ በክልሉ ከ700 በላይ የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሀብቶች የእርሻ ኢንቨስትመንት ፈቃድ መውሰዳቸውን ጠቁመዋል።

የክልሉ ኢንቨስትመንት ቦርድ ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ የኢንቨስትመንት እርሻ መሬት ተቀብለው ያላለሙ 54 ባለሀብቶች ሙሉ ለሙሉ በመሰረዝ 28 ሺህ 630 ሄክታር መሬት ወደ መሬት ባንክ ገቢ እንዲደረግ መወሰኑን አስታውቀዋል።

ፈቃዳቸው የተሰረዘባቸው ባለሀብቶች መሬት ተረክበው ወደ ስራ ያልገቡ፣ ስራ ጀምረው ያቆሙና የመሬት መጠቀሚያ ግብር ያልከፈሉ መሆናቸውንም ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.