Fana: At a Speed of Life!

ቻይና በዓለም ትልቁን የትራንስፖርት ማሳለጫ ገነባች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና በዓለም ትልቁን የትራንስፖርት ማሳለጫ በከፍተኛ ወጪ መገንባቷ ተመላክቷል፡፡

የቻይና የማሳለጫ መንገዶች ርዝማኔ በፈረንጆቹ 2023 ከ6 ሚሊየን ኪሎ ሜትሮች በላይ ማደጉ ተገልጿል፡፡

ይህም በዓለም ትልቁ የፍጥነት ባቡር፣ የፈጣን መንገድ ኔትወርክ፣ የፖስታ ኤክስፕረስ ማከፋፈያ አውታር እና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የወደብ መገልገያ ትስስር ያለው መሆኑን የትራንስፖርት ሚኒስቴር አመልክቷል።

የሀገሪቱ የትራንስፖርት ዘርፍ ፈጣን እድገት በማስመዝገብ ለቻይና ኢኮኖሚ እድገት መሰረት የሆነውን ጠንካራ የትራንስፖርት አገልግሎት በማቀጣጠል ላይ እንደሚገኝም ነወ የተገለጸው።

በፈረንጆቹ 2023 ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ያሳየው ዘርፉ÷ 3 ነጥብ 91 ትሪሊየን ዩዋን ወይም 539 ቢሊየን ዶላር ቋሚ የንብረት ኢንቨስትመንት ዕድገት ማሳየቱ ተመላክቷል፡፡

በዚህም ዘርፉ ከዓመት ወደ ዓመት 1 ነጥብ 5 በመቶ እድገትን እያሳየ መሆኑን ጠቁሟል።

በፈረንጆቹ 2023 መገባደጃ ላይ ቻይና 159 ሺህ ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውና ከዚህም ውስጥ 45 ሺህ ኪሎ ሜትሩ ለፈጣን ጉዞ የተወሰነ በዓለም ትልቁን የባቡር መስመር ዘርግታለች።

የሀገሪቱ የመንገድ አውታር መስፋፋትም 5 ነጥብ 44 ሚሊየን ኪሎ ሜትር የደረሰ ሲሆን÷ ከዚህም ውስጥ 183 ሺህ 600 ኪሎ ሜትር የሚሆኑት ነፃ ጎዳናዎች መሆናቸውን የሲጂቲኤን ዘገባ አመላክቷል።

በተጨማሪም ቻይና በ2023 አምስት አዳዲስ የንግድ አውሮፕላን ማረፊያዎችን በማከል አጠቃላይ ድምሩን 259 ማድረሷ ተጠቁሟል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.