Fana: At a Speed of Life!

አቶ አሻድሊ ሃሰን የክልሉን ጸጋ ወደ ልማት እየቀየርን ነው አሉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰላምን በማስጠበቅ የክልሉን ጸጋ ወደ ልማት የመቀየር ሥራ እየተሠራ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አሻድሊ ሃሰን ገለጹ።

የሌማት ትሩፋት ሥራን በጠንካራ ክትትል መተግበር በመቻሉ በአጭር ጊዜ አበረታች ውጤት መገኘቱን አቶ አሻድሊ ለፋና ብሮድካስንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

በክልሉ ከሚገኙ የሕብረተሰብ ልማት ፕሮጀክቶች መካከል “ህልዋ አግሮ ኢንዱስትሪ” አንዱ መሆኑን ጠቅሰው÷ የሰላም ችግር ለክልሉ ልማት እንቅፋት እንዳይሆን እየተሠራ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

በክልሉ የእንስሳት ዕርባታ፣ የንብ ማነብ እና ዓሣ ልማትን ጨምሮ የተለያዩ የልማት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡

የሕብረተ ሰብ ልማት ፕሮጀክቱ በክልሉ መንግሥት እየተተገበረ መሆኑን ጠቁመው በቀጣይ የግሉ ዘርፍ እንዲያለማ ሰፊ ዕድል ተመቻችቷል ብለዋል፡፡

“በክልሉ ያለውን ጸጋ ለይቶ ወደ ውጤት መቀየር” የሚል እሳቤ ያለው ፕሮጀክቱ÷ በክልሉ የእንስሳት ተዋጽዖን ጨምሮ የአትክልት ዋጋን ለማረጋጋት ዓልሞ እየሠራ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

የሥራ ዕድልና ተነሳሽነትን መፍጠሩንም ነው ያመላከቱት፡፡

በፍሬሕይወት ሰፊው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.