1 ሺህ 172 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 172 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።
የዛሬ ተመላሾች ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ÷ከእነዚህ ውስጥም 2 ጨቅላ ሕጻናትና ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ 29 ታዳጊዎች አንደሚገኙ ተገልጿል፡፡
ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን ድጋፍና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ሥራ እየተከናወነ መሆኑንም የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡