የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር የጦር ካቢኔያቸውን በተኑ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የሀገሪቱን ጦር ካቢኔ መበተናቸው ተሰምቷል፡፡
ውሳኔው የእስራኤል የጦር ካቢኔ ሚኒስትር ቤኒ ጋንትዝ ሥልጣን መልቀቃቸውን ተከትሎ የተደረገ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
የጦር ካቢኔው መበተን ውሳኔ የእስራኤል የፖለቲካ እና ደህንነት ካቢኔ በጉዳዩ ላይ ከመከረ በኋላ የተላለፈ መሆኑንም አልጀዚራ ዘግቧል፡፡
የእስራኤል ጦር ካቢኔ ስድስት አባላት የነበሩት ሲሆን÷ በቅርቡም አዲስ ካቢኔ እንደሚቋቋም ተጠቁሟል፡፡
በቅርቡ የጦር ካቢኔ ሚኒስትር ቤኒ ጋንትዝ ከስልጣን መልቀቅ ከጋዛ ጦርነት በኋላ ባለው ዕቅድ ላይ ከጠ/ሚ ቤንያሚን ኔታንያሁ ጋር የተፈጠረው ልዩነት ማሳያ ተደርጎ ሲነሳ መቆየቱ በዘገባው ተጠቅሷል፡፡