በኦሮሚያ ክልል ከ20 ሺህ በላይ ፕሮጀክቶች ተጠናቀዋል
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዘንድሮ በጀት ዓመት በኦሮሚያ ክልል ከ79 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ
የተደረገባቸው 20 ሺህ 664 አዲስና ነባር ፕሮጀክቶች መጠናቀቃቸውን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አወሉ አብዲ ገለጹ።
በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ተገንብተው የተጠናቀቁና ፕሮጀክቶችን አስመልክቶ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አወሉ አብዲ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።
አቶ አወሉ በመግለጫቸው እንዳስታወቁት፤ ፕሮጀክቶቹ የተገነቡት በመንግስት፣ በህብረተሰብ ተሳትፎና በአጋር አካላት ነው።
የመንገድ፣ የውሃ፣ የጤና ተቋማትና የትምህርት ቤቶች ግንባታ መካሄዱን ጠቅሰው፤ በዚህም ከ35 ሚሊየን በላይ ዜጎች ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልፀዋል።
ፕሮጀክቶቹ እስከ ሀምሌ አጋማሽ ድረስ በሁለቱ ዙር የሚመረቁና አገልግሎት የሚጀምሩ መሆናቸውንም ምክትል ርዕሰ መስተዳደሩ አስታውቀዋል።
በመራኦል ከድር