አዳማ ከተማ ሀዋሳ ከተማን በሰፊ የጎል ልዩነት አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አዳማ ከተማ ሀዋሳ ከተማን 5 ለ 0 በሆነ ሰፊ የጎል ልዩነት አሸነፈ።
በፕሪሚየር ሊጉ 27ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ቀን 9 ሠዓት ላይ ሐዋሳ ከተማ እና አዳማ ከተማ ጨዋታቸውን አድርገዋል፡፡
የአዳማ ከተማ የማሸነፊያ ጎሎችን ነቢል ኑሪ፣ ዮሴፍ ታረቀኝ 2 ጎሎችን፣ ቢኒያም ዐይተን እና አህመድ ረሺድ ያስቆጠሩ ሲሆን፤ ዮሴፍ ታረቀኝና ቢኒያም አይተን በፍጹም ቅጣት ምት አንድ አንድ ጎል አስቆጥረዋል።
በተመሳሳይ 12 ሠዓት ላይ በተካሄደ ጨዋታ ሲዳማ ቡና አበባየሁ ዮሀንስ (ፍ) እና ማይክል ኪፕሮቪ ባስቆጠሯቸው ጎሎች ሀምበሪቾን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።