Fana: At a Speed of Life!

በ18 ከተሞችና 107 ወረዳዎች ከፍተኛ አመራሮች ምልከታዎችን አድርገዋል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 10 ወራት በመላ ሀገሪቱ በ18 ከተሞች፣ 107 ወረዳዎችና በ253 በላይ ቀበሌዎች ላይ ከፍተኛ አመራሮች ምልከታዎችን ማድረጋቸውን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ ተናገሩ፡፡

ይህ ክትትል ለተመዘገበው የማክሮ ኢኮኖሚው እድገት አስተዋፅኦ እንዳለው ሚኒስትር ዴኤታዋ ዛሬ በወቅታዊ ጉዳች ላይ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል፡፡

ጉብኝቱ ምን እየተሰራ ነው? ምን አይነት ድጋፍ ያስፈልጋል? የሚለውን ለመመልከት ያስቻለም መሆኑን አንስተው፤ ምልከታው ለቀጣዩ በጀት ዓመት እቅድ ዝግጅት ላይ ግብዓት ሆኖ የሚያገለግል ነው ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል የኑሮ ውድነት ጫናን ለማቃለል ከተወሰዱ እርምጃዎች መካከል የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር አንዱ መሆኑን ገልፀው፤ ባለፉት 10 ወራት ውጤት መታየት የጀመረበት መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ለአብነትም ባለፉት 10 ወራት 4 ነጥብ 9 ቢሊየን እንቁላል በመላ ሀገሪቱ ተመርቷል ነው ያሉት፡፡

ይህም በእንቁላል አቅርቦት ላይ የታየውን እድገት በሌላው የምግብ ፍጆታ ላይ ለመድገም እንደሚሰራም አመልክተዋል።

በሌላ በኩል ሀገራዊ ምክር ኮሚሽኑ የደረሰበትን ሂደት ያነሱት ሚኒስትር ዴዔታዋ፤ አሁንም መንግስት አስፈላጊ ድጋፍ ማድረጉን ይቀጥላል፡፡

መንግስት ለሰላም ያለውን ፅኑ አቋም ያስመሰከረበት ነጥብ ነፍጥ አንግበው መንግስትን በሃይል ለመጣል የሚንቀሳቀሱ ቡድኖች ወደ ሰላማዊ መንገድ መጥተው ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴን ለመቀላቀል ቢፈልጉ የሚስተናገዱበት ሀገራዊ አሰራር እንዳልነበር ጠቅሰዋል።

መንግስት ይህንን የሰላም አቋሙን በተግባር ለማረጋገጥ የአዋጅ ማሻሻያ ማደረጉን አስታውሰዋል፡፡

እንዲሁም የዘንድሮ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት በይፋ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በይፋ መጀመሩን አንስተው፤ 39 ሚሊየን ዜጎች በ14 ዋና ዋና የስምሪት መስኮች ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አመላክተዋል፡፡

በዚህም በገንዘብ 21 ነጥብ 5 ቢሊየን የዋጋ ተመን አለው ነው ያሉት፡፡

በፌቨን ቢሻው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.