Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ኢትዮጵያና በኦሮሚያ ክልል ቀጣናዊ ሠላምና ፀጥታ ዙሪያ ምክክር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ እና በኦሮሚያ ክልል ቀጣናዊ ሠላምና ፀጥታ ዙሪያ በአርባ ምንጭ ከተማ ምክክር ተካሂዷል።

በመድረኩ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ፣ አቶ ፍቃዱ ተሰማ በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ እና በሀገር መከላከያ ሠራዊት የደቡብ ዕዝ አዛዥ ሊተናል ጀኔራል ሰለሞን ኢተፋን ጨምሮ ሌሎች የክልሎቹ ከፍተኛ አመራሮች፣ የመከላከያ ሠራዊትና የፌደራል ፖሊስ አመራሮች ተገኝተዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ የጀመርነውን የልማትና የብልጽግና ጉዞ በስኬት ለማስቀጠል በቀጠናው አስተማማኝ ሰላምና ፀጥታ ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።

ቀጣናው ሠላምና ደህንነቱ ተጠብቆ እንዲቆይ ማስቻል ለአንድ አካል የሚተው እንዳልሆነ ገልጸው፤ የሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ሰላምና ፀጥታን በአስተማማኝ ደረጃ ለማረጋገጥ በቅንጅት መስራት አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል።

በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ በበኩላቸው በቀጠናው አስተማማኝ ሰላምና ፀጥታ ለማረጋገጥ የጋራ ዕቅድ አውጥቶ መስራትና መመራት አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በመድረኩ በቀጣይም ተከታታይነት ያለዉ ግንኙነት በመፍጠር በጋራ ተቀናጅተው እንደሚመሩት ከስምምነት መድረሳቸውን የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት መረጃ አመልክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.