Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ምስጋኑ በኢትዮጵያ የፈረንሳይና የእንግሊዝ ኤምባሲ ሃላፊዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር ሬሜ ማሪሾንና የእንግሊዝ ኤምባሲ ጉዳይ ፈጻሚ አንድሪው ጋር ተወያይተዋል፡፡

አምባሳደር ምስጋኑ ከፈረንሳዩ አምባሳደር ጋር ባደረጉት ውይይት ኢትዮጵያ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነትን በተሟላ መልኩ ተግባራዊ ለማድረግ ያላትን ቁርጠኝነት አስረድተዋል፡፡

ለአፈፃፀሙ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ድጋፍ እንደሚቀጥል ያላቸውን እምነት መግለጻቸውንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

ሁለቱ ወገኖች በቀጣናዊ የጋራ ጉዳዮች በተለይም የቀጣናውን ሰላምና መረጋጋት ለማረጋገጥ በትብብር የመሥራት አስፈላጊነት ላይ መክረዋል፡፡

በተመሳሳይ አምባሳደር ምስጋኑ ከእንግሊዝ ኤምባሲ ጉዳይ ፈጻሚ ጋር ባደረጉት ውይይት÷እንግሊዝ ለአዲስ አበባ ከተማ ኮሪደር ልማት ፕሮጀክት የምታደርገውን ድጋፍ አድንቀዋል።

ጉዳይ ፈፃሚው በበኩላቸው በኮሪደር ልማት ፕሮጀክቱ ያዩትን ለውጥ አወድሰዋል፡፡

ሁለቱ ወገኖች በጋራ የሁለትዮሽ እና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውም ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.