Fana: At a Speed of Life!

በሐረር ከተማዋን የሚመጥን እድገት እውን ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ነው- አቶ ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረር ከተማ እድሜዋን የሚመጥን እድገት እውን ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ተናገሩ።

ርዕሰ መስተዳድሩ የሐረር ከተማን ስትራቴጂክ የልማት እቅድ ለመምራት ከተቋቋመው ግብረሃይል ጋር ተወያይተዋል።

በዚሁ ወቅት ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ÷ሐረር ከተማን የሚመጥን እድገት እውን ለማድረግ በልዩ ሁኔታ ርብርብ እየተደረገ ነው ብለዋል።

ከዚህ ቀደም በከተማዋ ሲሰሩ የቆዩ ስራዎች በቅንጅት አለመሰራቱ በውጤታማነት ላይ ተፅዕኖ አሳድሮ መቆየቱን ጠቅሰው÷አሁን ላይ እየተከናወኑ የሚገኙ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎችን በቅንጅት አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተናግረዋል።

የመሠረተ ልማት ስራዎችን፣ መሬትን በፕላን መምራት፣ የግንባታ ፍቃድ እና ቁጥጥር ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል አስፈላጊ መሆኑን አመላክተዋል።

ከተማዋን ውብ፣ ጽዱ እንዲሁም ለነዋሪው እና ለጎብኚው ምቹ ለማድረግ እየተከናወኑ የሚገኘውን አበረታች ስራዎች ማጎልበት ይገባልም ብለዋል።

በሌላ በኩል በከተማዋ ጽዳትና ውበት ላይ ተፅዕኖ እያሳደረ የሚገኘው የውጪ ማስታወቂያ በአፋጣኝ ልጓም ሊበጅላቸው እንደሚገባም አንስተዋል፡፡

በየተቋሙ ተጀመረው ያልተጠናቀቁ የመሰረተ ልማት ዝርጋታዎችን በቀሪ የአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ማጠናቀቅ እንደሚገባም አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

ህገ ወጥ የጎዳና ንግድና አገልግሎት ስርአት ለማስያዝ የተጀመሩ ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ማለታቸውንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.