Fana: At a Speed of Life!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በ169 ሚሊየን ብር የተገነባ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን በ169 ሚሊየን ብር የተገነባውን የቡልድግሉ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል መርቀው ከፈቱ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ጊዜ እንደገለፁት÷ የክልሉ መንግስት በጤና ዘርፍ የሚሰጡ አገልግሎቶችን በማሻሻል የህብረተሰቡን እርካታን ለመጨመር እየሰራ ነው ።

በተጨማሪም የጤና ተቋማት ደረጃን በማሻሻል ለዜጎች የሚሰጡ የጤና እና ጤና ነክ አገልግሎት ተደራሽ በማድረግ ጤናው የተጠበቀ አምራች ዜጋን ለመፍጠር የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉም ብለዋል።

የጤና ተቋማትን መገንባት ብቻ ግብ አይደለም ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ÷ በሰው ሀይል እና በቁሳቁስ በማሟላት ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጥ ማድረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የሆስፒታሉ ስራ መጀመር የአካባቢውን ህብረተሰብ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመፍታትና የተገልጋይ እርካታን ለመፍጠር ያግዛል ማለታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.