Fana: At a Speed of Life!

ለምግብ ዋስትና መረጋገጥ የገጠር ልማታዊ ሴፍትኔት መርሐ-ግብር ጉልህ ሚና እንዳለው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግሥት የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ በሚያደርገው ጥረት የገጠር ልማታዊ ሴፍትኔት መርሐ-ግብር ጉልህ ሚና እንዳለው ተመላከተ፡፡

5ኛው የገጠር ልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም የ2016 በጀት ዓመት ሁለተኛው ዙር የመንግሥት እና ለጋሽ ድርጅቶች የጋራ የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ እየተካሄደ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

የግብርና ሚኒስትር ዴዔታ ፍቅሩ ረጋሳ (ዶ/ር) በግምገማው ላይ እንዳሉት÷ መንግሥት የዜጎችን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ በሚያደርገው ጥረት ልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ነው፡፡

የመድረኩ ዓላማም የዘርፉን የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈፃፀም በመገምገም በፌደራልና በክልል ደረጃ ሊፈቱ የሚችሉ ክፍተቶችን በመለየት የቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ መግባባት ለመፍጠር መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በኢትዮጵያ የአውሮፓ ሕብረት ተወካይ ቤትሪስ ኔሪ በበኩላቸው÷ 5ኛው ልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም የተፈጥሮ አደጋ፣ የፀጥታ አለመረጋጋት እና የገንዘብ እጥረት ተግዳሮቶች እንዳጋጠሙት አስታውቀዋል፡፡

በፕሮግራሙ የተሰማሩ አካላት ተግዳሮቶች ሳይበግሯቸው ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገባቸውን በመጥቀስ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ለተወጡ አካላትም ምሥጋና አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.