Fana: At a Speed of Life!

በኮምቦልቻ ከተማ የ #ጽዱኢትዮጵያ ንቅናቄ አካል የሆነ የጽዳት ሥራ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ #ጽዱኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄ አካል የሆነ የጽዳት ሥራ “ፅዱ ከተሞች ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ሐሳብ በኮምቦልቻ ከተማ ተካሂዷል፡፡

በምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የአማራ ክልል የከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ አሕመዲን መሐመድ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት÷ ጽዱ ከተሞች እንፍጠር ተብሎ እንደ ሀገር ንቅናቄው የተጀመረው ከተሞች ለነዋሪዎችም ሆነ ለጎብኝዎች ምቹ እንዲሆኑ በማሰብ ነው።

በቀጣይም ሕዝብን በማሳተፍ፣ የአሠራር ሥርዓትን በመዘርጋት እና የባለ ድርሻ አካላትን ቅንጅታዊ አሠራር በማጎልበት ዘላቂነት ያለው አረንጓዴ ከተሞችን መፍጠር እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ ወንድወሰን ልሳነ ወርቅ በበኩላቸው÷ ኮምቦልቻን ውብና ተመራጭ የኢንቨስትመንት መዳረሻ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

#ጽዱኢትዮጵያ ንቅናቄ ለከተሞች የቅንጦት ተግባር ሳይሆን መሠረታዊ ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.