Fana: At a Speed of Life!

ህጎችና ደንቦች የህዝቡን ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ በመሆናቸው ለተፈጻሚነታቸው መሰራት እንዳለበት ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወጡ ህጎችና ደንቦች የህዝቡን ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ በመሆናቸው ለተፈጻሚነታቸው መሰራት እንዳለበት የክልሉ ምክር ቤት ገለጸ።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የዞን፣ የወረዳና የቀበሌ ምክር ቤት አፈ ጉባኤዎች በ2016 በጀት ዓመት አፈፃፀም የመጀመሪያ ዙር የጋራ የምክክር ፎረም በዲላ ከተማ ተካሂዷል።

የክልሉ አፈ-ጉባኤ ፀሐይ ወራሳ በመድረኩ እንዳሉት÷ ምክር ቤቶች የህዝብ ሉዓላዊነት የሚረጋገጥበት ለህዝብ ተጠቃሚነት የሚመከርበት ተቋማት በመሆናቸው መጠናከር አለባቸው።

በክልል ደረጃ የወጡ ህጎችና ደንቦች የህዝቡን ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ በመሆናቸው ሁሉም ቋሚ ኮሚቴዎች ለተፈፃሚነታቸው ተግተው እንዲሰሩ አስገንዝበዋል።

ምክር ቤቶችን መደገፍና ማጠናከር የህዝብን የልማት ጥያቄ የመመለስ ጉዳይ እንደሆነ ተረድተው ሁሉም ባለድርሻ አካላት ልዩ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

በየጊዜው የምክር ቤቶችን ስራ መከታተልና መገምገም ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለውም አንስተው፤ በምክክር መድረክ ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመፈተሽ የማሻሻያ ርምጃ መወሰድ እንዳለበት ጠቁመዋል።

የብሔረሰቦች ምክር ቤትና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የጋራ የምክክር ጉባኤ ማድረጋቸው በክልሉ ውስጥ ለሚሰሩ ተግባራት ስኬት ትልቅ ሚና እንዳለውም በመድረኩ ተገልጿል፡፡

በታሪክነሽ ሴታ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.