ከ2ኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር ውይይት እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገራዊ ጥሪን ተከትለው ወደ ሀገር ቤት ከገቡ ሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ውይይት እየተካሄደ ነው።
ውይይቱ “ታሪካዊ መሰረትዎን ይወቁ” በሚል መሪ ሃሳብ ነው በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም እየተካሄደ የሚገኘው።
በመርሐግብሩ የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ ዳያስፖራዎች እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ÷ ዳያስፖራው በሀገሩ የተመለከተውን ለተቀረው ዓለም በማስተዋወቅ የአምባሳደርነት ሚናውን እንዲወጣ መልዕክት አሰተላልፈዋል።
ዳያስፖራው ሀገርና ባህሉን ከማወቅ ባለፈ በተግባር የተለያዩ የልማት ስራዎችን እያገዘ እንደሚገኝም ገልፀዋል።
ኢትዮጵያ በፈጣን የልማት መንገድ ላይ ትገኛለች ያሉት ከንቲባዋ ÷ዳያስፖራው ይህን ማስቀጠል፣ ማጠናከርና ማፅናት ላይ የራሱን አሻራ እንዲያኖር ጠይቀዋል፡፡
ዳር ሁኖ ከመመልከትና ከማኩረፍ ይልቅ በሀገራቸው መስተካከልና መሻሻል የሚገባቸው ጉዳዮች ካሉ በባለቤትነት ስሜት እንዲታረም ሊሰሩ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡
በመራኦል ከድር