ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትናንትናው ዕለት በአዘርባጃን ያደረጉትን ጉብኝት አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በማብራሪያቸውም በአዘርባጃን በተለይ የመንግስት ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ሙሉ በሙሉ በዲጂታል እየተሰጠ እንደሚገኝና ይህም የአገልግሎት አሰጣጡ ቀልጣፋና ምቹ እንዲሆን ማድረጉን መመልከታቸውን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት በተለያዩ ዘርፎች ውጤታማ የሆነ ሪፎርም ማድረጉን ያስታወሱት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ አሁን ደግሞ የመንግስት ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥን ሪፎርም የማድረግ ስራዎች ተጀምረዋል ብለዋል።
የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርምና ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን የማድረግ ስራ እየተካሄደ በመሆኑ በዚህ ረገድ ከአዘርባጃን ጋር በመስራት በዘርፉ ትልቅ ለውጥ ለማምጣት ጉብኝቱ እንደሚጠቅም መጥቀሳቸውንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በተለይ በስምንት የመንግስት ተቋማት ውስጥ አገልግሎት አሰጣጥን ዲጂታላይዝ ለማድረግ በሙከራ ደረጃ እየተተገበረ እንደሚገኝ ገልጸው÷ከአዘርባጃን የተገኘው ተሞክሮ ለተጀመረው ስራ እንደ ግብዓት እንደሚያገለግል ገልጸዋል።
የኢትዮጵያና የአዘርባጃን የሲቪል ሰርቪስ ተቋማት አብሮ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸውንም ጠቁመዋል።