Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)የዓባይ ወንዝ ድልድይን መረቁ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከአራት አመት ተኩል በፊት ግንባታው የተጀመረውንን የዓባይ ወንዝ ድልድይ መረቁ፡፡

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የፌደራል እና የክልሎች ርዕሳነ-መስተዳድሮችም ተገኝተዋል፡፡

ዛሬ የተመረቀው ዘመናዊ ድልድይ የ380 ሜትር ርዝመት እና 43 ሜትር ስፋት እንዳለው ተገልጿል፡፡

በሁለቱም የመንገድ ክፍል ባለሶስት መስመር የተሽከርካሪ መንገድን ብሎም በጎን የብስክሌት መጋለቢያ መስመር የተሰናዳለት ግዙፍ ድልድይ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

የባህርዳር ከተማ ታላቅ መለያ ምልክት እንዲሆን የተገነባው የዓባይ ወንዝ ድልድይ የአካባቢውን የኢኮኖሚ እድገት ብሎም የመገናኛ አውታር የሚያነቃቃ እንደሚሆንም ነው የተገለጸው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.