Fana: At a Speed of Life!

በመንግሥት በኩል በሥራዬ ላይ ተፅዕኖ አልተደረገብኝም- ኮሚሽኑ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በመንግሥት በኩል እስከ አሁን ተፅዕኖ እንዳልተደረገበት ገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአውሮፓ ከሚገኙ የዲፌንድ ኢትዮጵያ ታስክ ፎርስ አባላት ጋር በበይነ-መረብ ውይይት አካሂዷል፡፡

በውይይቱም ኮሚሽኑ ከመንግሥት ጫና ነፃ መሆኑን እና ምክክሩን የተመለከቱ ጥያቄዎች ተነስተዋል፡፡

ለጥያቄዎቹ ምላሽ የሰጡት የኮሚሽኑ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገብረስላሴ÷ እስከ አሁን በነበሩ ስራዎች ኮሚሽኑ ከመንግስት በኩል የደረሰበት ጫና የለም፤ ሙከራም አልተደረገበትም ብለዋል፡፡

11 ኮሚሽኖች አባል የሆኑበት ምክር ቤት መኖሩን እና ውሳኔዎች በምክር ቤቱ በኩል እየተወሰኑ ስራዎች በገለልተኛነት እየተከናወኑ መሆኑንም ነው ያስረዱት፡፡

ምክክሩ ሲጠናቀቀቅ የተገኘው ውጤት ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግ ጠቁመው÷ ምክረ ሐሳቡ ለአፈፃፀም ለመንግስት ይቀርባል ማለታቸውን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

በውጪ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያንም በግጭት ውስጥ ያሉ እና ሌሎች የተለየ ሐሳብ ይዘው የሚንቀሳቀሱ አካላት ወደ ምክክሩ እንዲመጡና የኮሚሽኑ ሥራ ስኬታማ እንዲሆን የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊ የዲፌንድ ኢትዮጵያ ታስክ ፎርስ አባላት በበኩላቸው÷ ለኮሚሽኑ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.