አቶ ጀማል አሕመድ ለ #ጽዱኢትዮጵያ 1 ሚሊየን ብር ለገሱ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጀማል አሕመድ ለ #ጽዱኢትዮጵያ በግላቸው 1 ሚሊየን ብር ለገሱ።
ለጽዱ ኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር 50 ሚሊየን ብር የማሰባሰብ የዲጂታል ቴሌቶን እየተካሄደ ነው፡፡
በንቅናቄውም የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ሠራተኞች እና በሥሩ ያሉ ድርጅቶች በድምሩ 64 ሚሊየን ብር ለግሰዋል።
የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጀማል አሕመድ በግላቸው 1 ሚሊየን ብር ለንቅናቄው አበርክተዋል፡፡
መላው ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተው ሂሳብ ቁጥር 1000623230248፣ በብሔራዊ ባንክ የዶላር አካውንት 0101211300016 እና በስዊፍት ኮድ NBETETAA የ“ጽዱ ጎዳና – ኑሮ በጤና” ንቅናቄ የቻሉትን አስተዋጽ በማድረግ ንቅናቄውን እንዲቀላቀሉ ተጠይቀዋል፡፡