በአፍጋኒስታን በጎርፍ አደጋ ከ300 በላይ ሰዎች ሕይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍጋኒስታን ከወትሮው በተለየ የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው የጎርፍ አደጋ ከ300 በላይ ሰዎችን ሕይወት መንጠቁ ተሰምቷል፡፡
በአየር ንብረት ለውጥ የመጣ ነው የተባለው ይህ የጎርፍ አደጋ ከ1 ሺህ በላይ ቤቶችን እንዳወደመም የተባበሩት መንግስታት አስታውቋል፡፡
የታሊባን ቃል አቀባይ ዛቢሁላህ ሙጃሂድ ፥ ዜጎችን ከአደጋው ለመታደግ በሥፍራው አስፈላጊው የነፍስ አድን ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በአፍጋኒስታን የተመድ ልዩ ዘጋቢ ሪቻርድ ቤኔት እንደገለጹት ፥ የጎርፍ አደጋው አፍጋኒስታን ለአየር ንብረት ለውጥ ቀውስ ተጋላጭ መሆኗን የሚያሳይ ነው፡፡
በዚህም ታሊባን እና የሚመለከታቸው የዓለም አቀፍ አጋር አካላት አፋጣኝ እርዳታ እና የረጅም ጊዜ እቅድ አንደሚያስፈልጋቸው አስገንዝበዋል፡፡
በተመሳሳይ ባሳለፍነው ሚያዝያ ወር በሀገሪቱ የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ ቢያንስ 70 ሰዎች ለሕልፈት መዳረጋቸውን አስታውሶ የዘገበው ሲቢኤስ ኒውስ ነው፡፡