አገልግሎቱ እና ማኅበሩ በጋራ ለመሥራት የመግባቢያ ሠነድ ፈረሙ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ደምና ኅብረ ኅዋስ ባንክ አገልግሎት እና የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሠነድ ተፈራረሙ።
የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር አሸናፊ ታዘበው (ዶ/ር) ሁለቱም ተቋማት ለትርፍ ያልተቋቋሙ የሰብዓዊ ሥራ ላይ የተሰማሩ በመሆናቸው ተቀራርበው መሥራታቸው የሚበረታታ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ስምምነቱ በደም አሰባሰብ ላይ የተሻለ ሥራ ለመሥራት እንደሚያግዝም አስገንዝበዋል፡፡
የማኅበሩ ምክትል ዋና ፀሐፊ አበራ ሉሌሳ በበኩላቸው÷ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ለሚያደርገው የሕይወት አድን ሥራ ከአገልግሎቱ ተግባር ጋር የሚገናኝ በመሆኑ ስምምነቱን አስፈላጊ ያደርገዋል ብለዋል፡፡
ሠነዱ በማኅበሩ ሥር በሚገኙ በጎ ፈቃደኞች አማካኝነት የደም ማስለገስ ሥራን ጨምሮ ሌሎች ተግባራትን በትብብር ለማከናወን እንደሚያስችልም አብራርተዋል፡፡
ዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ቀንን ምክንያት በማድረግም ከነገ ጀምሮ እስከ ግንቦት 8 የሚቆይ ሀገር አቀፍ የደም ልገሳ እና የበጎ አድራጎት መርሐ-ግብር መዘጋጀቱን አስታውቀዋል፡፡
በሃይማኖት ኢያሱ