አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቀጣይ ክፍተቶቻችንን በመሙላት ለሕዝባችን የገባነውን ቃል በተግባር ለማዋል የምንሠራ ይሆናል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር የ2016 የሦስተኛ ሩብ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ እያካሄደ ነው፡፡
የአሥተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የሕዝባችንን የኑሮ ጫና ለማቅለል እና የተጀመሩ ትላልቅ ፕሮጀክቶቻችንን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ አዳጊና ተደማሪ የሆኑ አዳዲስ ዕይታዎችን ተግባራዊ አድርገናል ብለዋል፡፡
ውጤታማ የሥራ ባህል በመከተል እንዲሁም የአመራር ቅንጅትን ይበልጥ በማጎልበት የተከተልነው መንገድ ውጤታማ አድርጎናል ሲሉም ገልጸዋል፡፡
በቀጣይም ክፍተቶቻችንን በመሙላት ለሕዝባችን የገባነውን ቃል በተግባር ለማዋል የምንሰራ ይሆናል ማለታቸውን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡