Fana: At a Speed of Life!

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በንግድ ሥርዓቱ ላይ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በንግድ ሥርዓቱ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት በትኩረት እየተሠራ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መሥተዳድር እንዳሻው ጣሰው ገለጹ፡፡

አቶ እንዳሻው ጣሰው ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ገብረ መስቀል ጫላ ጋር ባደረጉት ውይይት÷ በሰላምና ጸጥታ፣ ግብርና፣ ገቢ፣ ትምህርት፣ ጤና፣ ንግድ፣ ኢንቨስትመንት እና የሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ የክልሉ መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በአፈጻጸም ረገድ ውስንነት የተስተዋለባቸውን ጉዳዮች ውጤታማ ለማድረግም በትጋት እየተሠራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

አቶ ገብረ መስቀል በበኩላቸው÷ የሰላምና ጸጥታ፣ የኑሮ ውድነት፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ እና የመልካም አሥተዳደር ጉዳዮች ላይ በማተኮር በዘርፉ የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ መሥራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ እንደሚገባ ገልጸው÷ የሌማት ትሩፋት ሥራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ መናገራቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

ሕገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴን ለመቆጣጠር፣ አምራችና ሸማችም በቀጥታ እንዲገናኝ ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር እንደሚገባ በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.