Fana: At a Speed of Life!

ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ በሻሸመኔ ክላስተር የተሳታፊዎች ልየታ እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በኦሮሚያ ክልል ሻሸመኔ ክላስተር በምክክር ሂደቱ የሚሳተፉ የማህበረሰብ ክፍሎች ልየታ እያካሄደ ነው።

በክልሉ በአራት ክላስተሮች ተከፋፍሎ የተሳታፊ ልየታ ስራ እየተካሄደ ሲሆን÷ እስካሁን በ282 ወረዳዎች 5 ሺህ 94 ተሳታፊዎች ተለይተዋል ተብሏል።

ዛሬ በሻሸመኔ ክላስተር በተጀመረው የተሳታፊዎች ልየታ ባሌ፣ ምስራቅ ባሌ፣ ምስራቅ ቦረና፣ ጉጂና ምስራቅ ጉጂ አካባቢዎች ከ66 ወረዳዎች 1 ሺህ 56 ተሳታፊዎችን የመምረጥ ሂደት እስከ መጪው ቅዳሜ እንደሚከናወን ተገልጿል።

በዛሬው መድረክም ከ11 ወረዳዎች የተወከሉ 880 የህብረተሰብ ክፍል ተወካዮች አጀንዳ ለማሰባሰብ የሚወከሉ 176 ተወካዮችን እንደሚመርጡ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በመድረኩ የምክክር ኮምሽኑ ኮሚሽነሮች የተገኙ ሲሆን÷ በኮሚሽኑ አስፈላጊነትና ሂደት ላይ ገለጻ እንደሚደረግም ተመላክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.