ደስታ የተሰኘችው ሮቦት በሳይንስ ሙዚየም ለእይታ ቀረበች
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ከአይኮግ ላብስ፣ ከኢትዮ ቴሌኮም፣ ከኢትዮጵያ አየር መንገድና ከራይድ ጋር በመተባበር ደስታ የተሰኘች ሮቦት በሳይንስ ሙዚየም ለእይታ አቅርበዋል።
አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ አሁን ላይ የደረሰበትን ደረጃ ለማሳየትና በኢትዮጵያ ምን አይነት ስራ እየተሰራ ነው የሚለውን ለማሳየት ሮቦቷ ለእይታ እንደቀረበች ተገልጿል፡፡
እንዲሁም ታዳጊ ልጆች ዘርፉ ምን ላይ እንዳለ እንዲገነዘቡና ወደ ፊት እነሱም በዘርፉ ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማድረግ ታልሞ ደስታ ሮቦት እንደቀረበች ተነግሯል።
በተጨማሪም ደስታ ሮቦት በተቋማቱ ባለሙያዎች በተደረገላት ፕሮግራም መሠረት በአማርኛ ቋንቋ ስለመጪው ዘመን የአርቴፊሻል ተስፋና ውጤት ጭምር ንግግር ለታዳሚው አድርጋለች።
በዓለምሰገድ አሳዬ