የኢድ ሶላት ስነ ስርዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 1 ሺህ 445ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል ሶላት ስነ ስርዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም ተካሂዷል፡፡
የእምነቱ ተከታዮች ከማለዳው ጀምሮ ወደ አዲስ አበባ ስታዲየም በመምጣት በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስርአቶች ሶላቱን አከናውነዋል፡፡
የረመዳን ጾም መጠናቀቁን ተከትሎ በዓሉ የሚከበር ሲሆን÷ከሶላት ስነ ስርዓቱ በኋላ የእምነቱ አስተምህሮ በሚያዘው መሰረት የእምነቱ ተከታዮች በዓሉን የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳትም ያከብራሉ።
በመራዖል ከድር