Fana: At a Speed of Life!

ቻይና ለኢትዮጵያ አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ የምታደርገውን ድጋፍ እንደምታጠናክር ገለጸች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዛኦ ዚዩዋን ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ÷ በኢንዱስትሪ ዘርፍ የሁለቱን ሀገራት ትስስር ይበልጥ በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

ቅባቱ የወጣለት የአኩሪ አተር ምርት ኤክስፖርት፣ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችና የትምህርት እድሎች በተለይም የልህቀት ማዕከላት ግንባታ ላይ ተወያይተዋል፡፡

አቶ መላኩ አለበል ÷ መንግስት በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ መዋቅራዊ ሽግግር እና ኢንዱስትሪያላዜሽን ለማምጣት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን አንስተዋል፡፡

አምባሳደር ዛኦ ዚዩዋን በበኩላቸው÷ በኢትዮጵያ እና ቻይና መካከል ጠንካራ ግንኙነት እንዳለ መግለጻቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

የሁለትዮሽ ግንኙነቱን ይበልጥ ለማጠናከር ቻይና በተለይም ለኢትዮጵያ ኢንዱትሪያላያዜሽን እድገት የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.