አሜሪካ በግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ አፕል ላይ ክስ መሰረተች
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ‘አፕል’ የስማርትፎን ገበያውን በብቸኝነት እየተጠቀመ ነው ስትል አሜሪካ ከሳለች።
የአሜሪካ ፍርድ ቤት ባቀረበው ክስ÷ ኩባንያው የአይፎን ተጠቃሚዎች ወደ መተግበሪያው እንዴ ከገቡ በኋላ እንዳይወጡ በመቆለፍ ያለፍላጎታቸው ደንበኛ እንዲሆኑ ማስገደዱን ገልጿል፡፡
በተለይም ኩባንያው ተወዳዳሪ መተግበሪያዎች ወደ ገበያው በሚገቡበት ጊዜ እንዲከሽፉ በማደረግ እና የራሱ መተግበሪያዎች ብቸኛ አማራጭ ሆነው እንዲቀርቡ ለማድረግ ህገ ወጥ እርምጃዎችን መዉሰዱን ጠቁሟል፡፡
ግዙፍ የሆኑ ኩባንያዎች ሌሎች ተፎካካሪዎች በገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ማበረታታት እንደሚገባ የሚፈቅደውን ህግ አፕል ኩባንያ በመጣሱ የኩባንያው ደንበኞች የአፕል መተግበሪያዎችን በውድ ዋጋ እንዲገዙ መገደዳቸውን በክሱ ተጠቅሷል።
አፕል በበኩሉ ደንበኞቹ ለረጅም ጊዜ የኩባንያው ምርት ተጠቃሚ በመሆናቸው ደስተኛ እንደሆኑ ገልፆ፤ በአሜሪካ ህግ መሰረት ደንበኞች የፈለጉትን ኩባንያ መተግበሪያ መጠቀም እንደሚችሉ ጠቅሷል።
በመሆኑም አፕል የቀረበበትን ክስ እንደማይቀበለው በመግለጽ፤ ክሱን አጥብቆ እንደሚቃወመው ማስታወቁን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡