Fana: At a Speed of Life!

ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ የዜጎችን ፍትሐዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የጎላ ፋይዳ እንዳለው ገለጹ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ የዜጎችን ፍትሐዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ፋይዳው የጎላ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም አሁናዊ ሁኔታና የወደፊት ዕቅዶችን አስመልክቶ በብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዋና መስሪያ ቤት ተገኝተው ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝታቸው ወቅት ባደረጉት ንግግርም÷ ብሔራዊ መታወቂያ ከዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ውስጥ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ አስቻይ ስትራቴጅዎች ውስጥ አንዱ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ የዜጎችን ፍትሐዊ ተጠቃሚነት እና አገልግሎት የማግኘት ቅልጥፍናን ለማረገጥ አይነተኛ ሚና እንደሚጫወትም ነው ያስገነዘቡት፡፡

የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ተጠቃሚ መሆን ለእያንዳንዱ ዜጋ አስፈላጊ መሆኑንም በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

ለዚህም መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል ማድረጉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

ከጉብኝታቸው በኋላም የብሔራዊ መታወቂያ ለመውሰድ የሚያስችላቸውን ምዝገባ አከናውነዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.