Fana: At a Speed of Life!

የክልሉን ህዝብ ከልማት ስብራቶች ለማላቀቅ የሥራ እድል ፈጠራ ላይ ማተኮር ይገባል- አቶ አረጋ ከበደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የክልሉን ህዝብ እየገጠመው ካለው የኢኮኖሚ ልማት ስብራቶች ለማውጣት የሥራ እድል ፈጠራ ላይ በትኩረት መሥራት ይገባል ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ተናገሩ፡፡

ርዕሰ መሥተዳድሩ ከኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ሁሉም አካባቢዎች ከተውጣጡ የማህበረሰብ ተወካዮች ጋር እየተወያዩ ነው።

ክልሉን ለማፍረስ የሴራ ተግባራቸውን እየፈፀሙ ያሉ የጥፋት ሀይሎችን ለመከላከል በተሠራው ሥራ በርካታ አካባቢዎችን ወደ አንፃራዊ ሰላም መመለስ መቻሉን ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ በመድረኩ ገልጸዋል።

ሕዝቡ የኢኮኖሚ ልማትና የማኅበራዊ ልማት ስብራቶች እንዳሉበት በመግለፅም በተለይ የወጣቶች የሥራ እድል ፈጠራ ላይ በትኩረት መሥራት ይጠይቃል ብለዋል።

በውይይት መድረኩ ከርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በተጨማሪ ሌሎች የክልሉና የብሔረሰብ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች መገኘታቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.