‹‹የዲጂታል ኢትዮጵያ ሣምንት›› ከነገ ጀምሮ ሊካሄድ ነው
አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመጀመሪያው ‹‹የዲጂታል ኢትዮጵያ ሣምንት›› ከየካቲት 18 እስከ 22 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ለአምስት ቀናት እንደሚካሄድ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
መርሐ-ግብሩ የሚካሄደው “የጋራ ጥረታችን ለዲጂታል ኢትዮጵያችን” በሚል መሪ ሐሳብ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ዝግጅቱ የኢትዮጵያን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ሥራዎች ለማኅበረሰቡ ለማስተዋወቅ ያለመ ነው ተብሏል፡፡
በተጨማሪም ኅብረተሰቡ የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን እንዲጠቀም ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡
በመርሐ-ግብሩም÷ የኤሌክትሮኒክ መንግሥት ስትራቴጂ ዎርክሾፕ፣ የመንግሥት ኢንተርፕራይዝ አርክቴክቸር ዎርክሾፕ፣ የዲጂታል ኢትዮጵያ ፓናል ውይይት እና ሀገራዊ የዲጂታል አቅሞች ምልከታ የሚከናወን እንደሚከናወን ተጠቅሷል፡፡