Fana: At a Speed of Life!

የሐረሪ ክልል ምክር ቤት ጉባኤ የተለያዩ ሹመቶችን በማፅደቅ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ ሹመቶችን በማፅደቅ ተጠናቀቀ።

ምክር ቤቱ በጉባኤው የክልሉን ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ ሮዛ ዑመር ሹመትን አጽድቋል፡፡

ወ/ሮ ሮዛ በምክር ቤቱ ቀርበው ቃለ ማሃላ ፈፅመዋል።

በተጨማሪም ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው ጉባኤ በክልሉ ባለፉት ስድስት ወራት የተከናወኑ ተግባራትን በተመለከተ በርእሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ የቀረበውን ሪፖርት ተወያይቶ አፅድቋል፡፡

በተሾመ ኃይሉ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.