Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከብራዚል ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከብራዚል ፕሬዚዳንት ሉዊዝ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ ጋር ተወያዩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ዛሬ ለይፋዊ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የመጡትን የብራዚል ፕሬዚዳንት ሉዊዝ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫን ተቀብያለው ብለዋል።

በውይይታችንም የግንኙነታችንን ጥልቀት የሚያንፀባርቁ የተለያዩ የሁለትዮሽ እና ባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገናል በማለት ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ የተከበረው የብሪክስ ቡድን አባል ሆና በመቀላቀሏ ከብራዚል ጋር ያለን ግንኙነት የበለጠ እንደሚጠናከር እንጠብቃለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ የዛሬው ግንኙነታችንም የፀና ወዳጅነት የመገንባት አንድ እርምጃ ነው ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.