Fana: At a Speed of Life!

ብሪክስ በፈረንጆቹ 2028 ቡድን ሰባት ሀገራትን በኢኮኖሚ ይበልጣል ተባለ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሪክስ አባል ሀገራት በሚቀጥሉት አራት ዓመታት ውስጥ ከቡድን ሰባት አባል ሀገራት በጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ድርሻ ብልጫ እንደሚኖራቸው የብሪክስ ልማት ባንክ ኃላፊ ዲልማ ሩሴፍ ገለጹ።
 
በዱባይ በተካሄደው የዓለም መንግስታት ጉባኤ ላይ የዓለም አቀፉ አበዳሪ ተቋም ሊቀ መንበር የብሪክስ አባል ሀገራትን የሀገር ውስጥ የምርት ዕድገት በተመለከተ ተናግረዋል፡፡
 
ኃላፊዋ በንግግራቸው አዳዲስ አባላት ሲጨመሩ የቡድኑ ድርሻ በፈረንጆቹ 2028 አሁን ካለበት 35 በመቶ ወደ 40 በመቶ እንደሚደርስና የቡድን ሰባት የበለጸጉ ሀገራት ድርሻ ደግሞ ወደ 27 ነጥብ 8 በመቶ እንደሚቀንስ ጠቁመዋል።
 
ሩሴፍ አክለውም በዓለም አቀፉ ንግድ የብሪክስ ድርሻ በፈረንጆቹ 2016 ከነበረበት 37 በመቶ በ2022 ወደ 41 በመቶ ያደገ ሲሆን ቡድን ሰባት ግን ድርሻው ከ62 በመቶ ወደ 58 በመቶ ቀንሷል ማለታቸውን አር ቲ ዘግቧል።
 
ቀደም ሲል ብራዚልን፣ ሩሲያን፣ ህንድን፣ ቻይናን እና ደቡብ አፍሪካን ያቀፈው የብሪክስ ቡድን ሳውዲ አረቢያ፣ ኢራን፣ ኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ከተቀላቀሉት በኋላ መስፋፋት ማሳየቱ ተመላክቷል።
 
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.