Fana: At a Speed of Life!

በኮንጎ ወንዝ ሁለት ጀልባዎች ተጋጭተው በርካቶች ሞቱ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ኪንሻሳ አቅራቢያ በኮንጎ ወንዝ ውስጥ ሁለት ጀልባዎች ተጋጭተው በርካታ ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች መጥፋታቸው ተገለጸ፡፡

ሰዎችንና ሸቀጦችን ጭነው ሲጓዙ በነበሩ ሁለቱ ጀልባዎች መካከል በተከሰተው የመጋጨት አደጋ ምን ያህሉ በህይዎት እንደተረፉ አልታወቀም።

የአደጋው ምክንያት እስካሁን በግልጽ እንዳልታወቀም ተነግሯል።

አደጋው በደረሰበት ወቅት ይፋ በሆኑ ተንቀሳቃሽ ምስሎች ትናንሽ ጀልባዎች ተጎጂዎችን ለመታደግ ወደስፍራው ሲያመሩ ታይተዋል።

ምቹ ያልሆነ የመንገድ መሰረተ ልማት ባላት ሀገር ወንዞች ለመጓጓዣ ተመራጭና ቁልፍ መሆናቸው ይነሳል፡፡

መሰል የጀልባ አደጋዎች ደግሞ አብዛኛውን ጊዜ የሚከሰቱት ጀልባዎቹ ከመጠን በላይ ስለሚጭኑ እንደሆነም ነው አፍሪካ ኒውስ በዘገባው ያስነበበው።

አብዛኛው ጊዜ ወንዝ ላይ የሚካሄዱ የትራንስፖርት እንቅስቃሴዎች መደበኛ ባልሆኑ ኦፕሬተሮች እንደሚመራ የተጠቀሰ ሲሆን፥ የሀገሪቱ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የባህር ላይ ደንቦችን የማክበር ባህል ደካማ በመሆኑ ጥንቃቄ እንዲወሰድ አስጠንቀቀው ነበር።

#Congo #Kinshasa

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.