Fana: At a Speed of Life!

ተልዕኳቸውን በጀግንነት ፈጽመው ለተመለሱ ልዩ የፀረ-ሽብር አመራርና አባላት አቀባበል ተደረገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ተልዕኳቸውን በጀግንነት ፈጽመው ለተመለሱ ልዩ የፀረ-ሽብር አመራርና አባላት በኮልፌ ፈጥኖ ደራሽ ካምፕ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ልዩ ፀረ ሽብር መምሪያ አመራርና አባላት በተለያዩ ግዳጆች ላይ ከአራት ዓመት በላይ ቆይተው ሲመለሱ የወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ በተገኙበት ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡

የልዩ ፀረ-ሽብር አባላቱ የኦነግ ሸኔ የሽብር ቡድን በሚንቀሳቀስባቸው በምዕራብ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ምሥራቅ ወለጋ፣ ሆሮ ጉድሩ እና ምዕራብ ሸዋ ዞኖች እንዲሁም በሌሎች አካባቢዎች በተልዕኮ ላይ ቆይተው ለሌላ ፖሊሳዊ ተልዕኮ እንደተመለሱ ታውቋል፡፡

የልዩ ፀረ-ሽብር ኃይሉ ያካበተውን ልምድና ሙያዊ ብቃት ተጠቅሞ በተሰማራባቸው አካባቢዎች ሁሉ በፀረ-ሰላም ኃይሎች ላይ ሕጋዊ እርምጃ በመውሰድና በመቆጣጠር በርካታ ድሎችን ሲጎናፀፍ የቆየ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ልዩ ፀረ-ሽብር ኃይል አመራርና አባላቱም በቀጣይ የሚሰጣቸውን ተልዕኮ በጥሩ ፖሊሳዊ ሙያና ስነ-ምግባር ለመፈፀም የተዘጋጁ መሆናቸውን መግለጻቸውን ከፌዴራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.