Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውርን ለመግታት ከሐሳብ ያለፈ ዓለም አቀፍ ትብብር የለም አሉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውርን ለመግታት ከሐሳብ የዘለለ ዓለም አቀፍ ትብብር አለመኖሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
 
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 14ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ከሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ጋር በተያያዘ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
 
በማብራሪያቸውም ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር በጣም ትልቅ ችግር እንደሆነና በጉዳዩ ላይም በርካታ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አንስተዋል፡፡
 
የቴክኖሎጂውን ዘርፍ እና የባንክ አሠራርን ከማዘመን አንፃር የሪፎርም ሥራዎች ቢከናወኑም አሁንም ችግሩ መኖሩን ጠቅሰዋል፡፡
 
ምክንያቶችን ተገን በማድረግ መንግሥት ገንዘብ ከሀገር አያሸሽም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)÷ መንግስት ያገኘውን ገንዘብ ሁሉ በሀገር ውስጥ ልማት ላይ እያዋለ ነው ብለዋል፡፡
 
የሚታዩ ልማቶችም የዚህ ውጤት ማሳያ መሆናቸውን ነው ያስገነዘቡት፡፡
 
ይሁን እንጂ ግለሰቦች ባላቸው ግንኙነትና የተለያየ ስልት ተጠቅመው ገንዘብ የማዘዋወር ሥራቸውን እንዳላቆሙ ጠቁመው÷ ይህንን ተግባር ለመከላከል ተጨማሪ ሥራዎችን ማከናወን እንደሚያስፈልግ አመላክተዋል፡፡
 
ዓለም ስለ ሙስና ሲያብራራ፣ አፍሪካ እንዴት በሙስና ውስጥ እንደተዘፈቀች ሲገልፅ እና ሙስና እንዴት ፀረ ልማት እንደሆነ ሲተነትን እንጂ ከሙስና ጋር አልተባበርም ሲል አይተው እንደማያውቁም ገልፀዋል፡፡
 
ከማብራሪያ ባለፈም የሚሰረቀው ሁሉ ገንዘብ ወደ ተለያዩ ሀገራት ሲወሰድ ከየት እንደመጣ እየታወቀ ይህ የሌብነት ገንዘብ ነው ብሎ ለመመለስ ትብብር ሲደረግ እንደማይታይም ጠቁመዋል፡፡
 
በመሆኑም ትብብሩ ከሐሳብ በዘለለ ወደ ተግባር የገባ ባለመሆኑ በዚህ ረገድ እስከ አሁን የታየ ለውጥ አለመኖሩን አያይዘው ገልጸዋል፡፡
 
በታምራት ቢሻው
 
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.