የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም አንድነታችንን የምናጠናክርበት ነው- አፈ-ጉባዔ ታገሰ
አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የጋራ ታሪካችንን በመዘከር አንድነታችንን የምናጠናክርበት ነው ሲሉ አፈ-ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ ተናገሩ፡፡
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ታገሰ ጫፎን እና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየምን ጎብኝተዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አሥተደደር ከንቲባ አዳነች አቤቤም የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ፕሮጀክትን በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል።
በገለጻቸውም ከፕሮጀክቱ ጅማሬ እስከ ፍፃሜ ድረስ ለተሳተፉና ዐሻራቸውን ላስቀመጡ ሁሉ ምስጋና ማቅረባቸውን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡
ከገለጻው በኋላም አፈ-ጉባዔ ታገሰ ባደረጉት ንግግር÷ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ሀገራዊ የጋራ ታሪካችንን በመዘከር አንድነታችንን የምናጠናክርበት እና የወደፊት ብልጽግናችንን የምናረጋግጥበት ነው ብለዋል፡፡