Fana: At a Speed of Life!

የኤሌክትሪክ አገልግሎት መልሶ ግንባታ ሥራ በ10 ከተሞች ሊጀመር ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ10 ከተሞች የኤሌክትሪክ አገልግሎት መልሶ ግንባታና የኃይል አቅም የማሳደግ ሥራ ከያዝነው ዓመት አንስቶ ሊጀመር መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡

ከአሥሩ የክልልና የዞን ከተሞች መካከልም ጅግጅጋ እና አሶሳ ከተሞች እንደሚገኙበት የአገልግሎቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሽፈራው ተሊላ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ የ72 ከተሞችን የኃይል አቅም የማሳደግ ሥራ በቀጣይ እንደሚሠራ ጠቁመው÷ አሁን ላይም የጥናት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

በዙፋን ካሳሁን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.