Fana: At a Speed of Life!

በፈረንጆቹ 2023 በሩሲያ የውጭ ጎብኚዎች ቁጥር በ3 እጥፍ አድጓል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከዩክሬን ጋር በገባችው ጦርነት ምክንያት ምዕራባውያን ማዕቀቦች ቢጥሉም በፈረንጆቹ 2023 የውጭ ጎብኚዎች ቁጥር ከፍተኛ ጭማሪ ማሳየቱን የሩሲያ የደኅንነት አገልግሎት አስታውቋል፡፡
 
ጎብኚዎችን ጨምሮ ወደ ሩሲያ የሚገቡ የውጭ ሀገር ዜጎች አጠቃላይ ቁጥር በ2023 በ18 ነጥብ 6 በመቶ መጨመሩንም ነው የአገልግሎቱ መረጃ ያመላከተው፡፡
 
በ2023 የውጭ ዜጎች የሩሲያን ድንበር 15 ነጥብ 4 ሚሊየን ጊዜ ያቋረጡ ሲሆን÷ ይህም በ2022 ከተመዘገቡት አሃዞች በሦስት እጥፍ ብልጫ ማሳየቱ ነው የተገለጸው፡፡
 
ከአብዛኛዎቹ ጎብኝዎች አንድ ሦስተኛውን ድርሻ የሚወስዱት የቻይና ዜጎች መሆናቸው ናቸው ተብሏል፡፡
 
ይህም ለቡድን ጉብኝት ከቪዛ ነፃ የሆነ ሥርዓት መጀመሩን ተከትሎ የተገኘ ውጤት መሆኑ ተጠቅሷል፡፡
 
ወደ ሩሲያ ለጉብኝት ጉዞ ካደረጉ ቀዳሚ አምስት ሀገራት መካከልም ቁጥራቸው በሁለት እጥፍ የጨመረው÷ የጀርመን፣ ቱርክ፣ የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች እና የቱርክሜኒስታን ዜጎች መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡
 
በፈረንጆቹ 2024 የጎብኝዎች ቁጥር በአራት እጥፍ ሊያድግ እንደሚችል መተንበዩንም አርቲ ዘግቧል፡፡
 
ለዕድገቱ መጨመርም የሩብል ምንዛሪ አነስተኛ መሆን እና የኤሌክትሮኒክ ቪዛ ወደ ሥራ መግባት እንደምክንያት ተነስቷል፡፡
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.