በናይሮቢ በደረሰ የጋዝ ፍንዳታ ቢያንስ የሶስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ከ300 በላይ ቆሰሉ
አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ በደረሰ ከፍተኛ የጋዝ ፍንዳታ ሦስት ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ በትንሹ 300 የሚሆኑ ሰዎች ቆስለዋል።
በኤምባካሲ ወረዳ ጋዝ የጫነ ከባድ ተሸከርካሪ ላይ በደረሰ ፍንዳታ የእሳት አደጋ መከሰቱን የመንግስት ቃል አቀባይ አይዛክ ሙዋራ ሙዋራ ተናግረዋል።
በቃጠሎውም በአፓርታማዎች አቅራቢያ የሚገኙ የመኖሪያ ቤቶች፣ የንግድ ድርጅቶች እና ተሸከርካሪዎች መውደማቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
የኢምባካሲ ፖሊስ አዛዥ ዌስሊ ኪሜቶ በፍንዳታው ከሞቱ ሰዎች መካከል አንድ ሕፃን እንደሚገኝ ገልጸው፤ የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ጠቁመዋል።
የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
የኬንያ ቀይ መስቀል በበኩሉ 271 ሰዎችን ወደ ሆስፒታል እንደወሰደና 27 ሰዎችን በቦታው ማከም መቻሉን ገልጿል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!