Fana: At a Speed of Life!

ምሽቱን የተካሄዱ የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ 5 ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀቁ

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኮቲዲቯር አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ በተመሳሳይ ሰዓት ምሽት ላይ የተካሄዱ የምድብ አምስት ሁለት ጨዋታዎች ያለምንም ጎል በአቻ ውጤት ተጠናቅቀዋል፡፡

ናሚቢያ ከማሊ እንዲሁም ደቡብ አፍሪካ ከቱኒዚያ ያደረጉት ጨዋታ ያለምንም ጎል በአቻ ውጤት ተጠናቅቋል፡፡

ይህን ተከትሎም ማሊ በ5 ነጥብ እንዲሁም ደቡብ አፍሪካ እና ናሚቢያ በእኩል 4 ነጥብ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፋቸውን አረጋግጠዋል፡፡

በአንጻሩ ቱኒዚያ በ2 ነጥብ ከ34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውጭ ሆናለች፡፡

የምድብ 6 የመጨረሻ ጨዋታዎች መካሄዳቸውን ሲቀጥሉ ምሽት 5፡00 ሠዓት ላይ÷ ዛምቢያ ከሞሮኮ እንዲሁም ታንዛኒያ ከዲሞክራቲክ ኮንጎ ይፋለማሉ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.