Fana: At a Speed of Life!

በጽንፈኛው ላይ እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች ይቀጥላሉ – ሌ/ጄ ብርሃኑ በቀለ

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጽንፈኛው ላይ እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የሰሜን ምዕራብ ዕዝ አዛዥና የቀጣናው ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ ገለጹ፡፡

የቀጣናውን አሁናዊ ሁኔታ አስመልክቶ በተልዕኮ አፈፃፀም፣ በተገኙ ውጤቶችና በቀጣይ የዘመቻ ስምሪቶች ላይ በጎንደር ከተማ ውይይት ተደርጓል።

ሌተናል ጄኔራል ብርሀኑ በውይይቱ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ሕብረተሰቡን ያሳተፈ የቅንጅት ሥራ በመሥራት ጽንፈኛውን ኃይል ትርጉም ወደሌለው ደረጃ ማድረስ ይገባል ብለዋል፡፡

የአመራር አካላትንና የፀጥታ መዋቅሩን አቅም ከመገንባት አንፃር ውጤታማ ሥራዎች ተሠርተዋል ማለታቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡

የዞንና የወረዳ አመራሩ እንዲሁም የፀጥታ መዋቅሩም ከሕብረተሰቡ ጋር በጋራ በመሥራት የበለጠ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚጠበቅበት አስገንዝበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.